ዩኒቲ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ ከ1700 በላይ ተማሪዎችን ያስመርቃል
ዩኒቲ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ ለ22ኛ ጊዜ በመደበኛና በርቀትና ተከታታይ ትምህርት በዲግሪ፣ በዲፕሎማና በ10+3 ዲፕሎማ በቀንና በማታ ያስተማራቸውን ከ1700 በላይ ተማሪዎችን በአዲስ አበባ በኤግዚቢሽን ማዕከል ቅዳሜ ሐምሌ 28 ቀን 1999 ዓ.ም. ከጠዋቱ 2፡00 ሰዓት ጀምሮ ያስመርቃል፡፡
ከዩኒቨርሲቲ ኮሌጁ ኮርፖሬት ኮሚዩኒኬሽንስ ክፍል የወጣው መረጃ እንዳብራራው የዘንድሮዎቹ የዲግሪ ምሩቃን በአካውንቲንግ፣ በኢኮኖሚክስ፣ በማኔጅመንት፣ በማርኬቲንግ ማኔጅመንት፣ በማኔጅመንት ኢንፎርሜሽን ሲስተምስ፣ በኔትዎርኪንግ ኤንድ ዳታ ኮሚዩኒኬሽንስ፣ በሕግ፣ በአርክቴክቸርና ኧርባን ፕላኒንግ፣ በእንግሊዘኛና በስታትስቲክስ ሲሆኑ በ10+3 Ç=ýKAT ደግሞ በአካውንቲንግ፣ በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ፣ በሴልስማንሺፕ፣ በሰክሬተሪያል ሳይንስ፣ በሕግ፣ በጆርናሊዝምና ኮሚዩኒኬሽንስ፣ በፐርሶኔል ማኔጅመንት፣ በቢዝነስ አድምኒስትሬሽን፣ በማርኬቲንግ፣ በክሊኒካል ነርሲንግ፣ በላብራቶሪ ቴክኒሽያንና በፋርማሲ ቴክኒሽያን ሙያዎች የሚመረቁ ናቸው፡፡
ዩኒቲ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ በያዝነው ዓመት በርቀትና ተከታታይ ትምህርት ክፍሉ በስምንት የትምህርት ዓይነቶች ሙሉ የዲግሪ እውቅና አግኝቷል፡፡ ዘንድሮም በአካውንቲንግ፣ በኢኮኖሚክስ፣ በማኔጅመንት፣ በማርኬቲንግ ማኔጅመንት፣ በእንግሊዘኛና በስታትስቲክስ የትምህርት ዘርፎች ለመጀመሪያ ጊዜ በዲግሪ ያስመርቃል፡፡
Date 2007-07-31 08:11:35