Back to List 

ዩኒቲ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ የአዲስ ተማሪዎች ምዝገባ ጀመረ
ዩኒቲ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ የአዲስ ተማሪዎች ምዝገባ ጀመረ

 

ለ2000 ዓ.ም. ቅድመ እውቅና ባገኘባቸው የድኀረ-ምረቃ ኮርሶች በቢዝነስ አድሚኒሰትሬሽንና በዴቨሎፕመንት ኢኮኖሚክስ እንዲሁም ሙሉ እውቅና ባገኘባቸው የዲግሪ፣ የዲፕሎማና የሰርተፊኬት ፕሮግራሞቹ በሙሉ ምዝገባ መጀመሩን የዩኒቨርሲቲ ኮሌጁ ሬጅስትራር ቢሮ አስታወቀ፡፡

 

ፒያሳ በሚገኘው የዩኒቲ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ ካምፓስ የትምህርት ሚኒስቴርን የመግቢያ መስፈርት የሚያሟሉ በሙሉ በመረጡት የትምህርት መስክ ከሐምሌ 9 ቀን 1999 ዓ.ም. ጀምሮ ባሉት የሥራ ቀናት መመዝገብ እንደሚችሉ መግለጫው ጨምሮ ገልል፡፡

 

ዩኒቲ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ ምን ግዜም በጥራት የማስተማር ብቃቱ ከግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ፈር ቀዳጅ የሆነና ተመራጭ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ መሆኑን የገለፀው ይኼው የሬጅስትራር መግለጫ በመጪው ሚሊኒየም ዛሬም በትምህርት ጥራት ላይ እንደሚንቀሳቀስ አስገንዝቧል፡፡

Date    2007-07-16 16:41:21